top of page
Search
Writer's pictureMohammed Abaoli

በፖሎቲካው ለውጥ ጎዳና ላይ፤ የሙስሊሞቹ ዕጣ ፈንታ


ልክ እንደ ከ 1974ዎቹ በፊት የነበረው ስርዓት፤ አሁንም የኡለሞች ጭፍቸፋ እና መስጂዶችን ማቃጠል እንዲሁም ሙስሊሞችን በፖሎቲካ ስም ከምድር ገጽ ላይ የማጥፋት ዘመቻ ሞቅ ባለ መልኩ ተጀምረዋል። ያሳዝናል ያስለቅሳል!! ሙስሊም በበዛባት ሀገር ዲሞክራሲ አለ ተብሎ በሚወራባት ሀገር መስጂድ ማቃጠል፣ ኡለሞችን መግደል፣ ወጣቶችን መግደል እና ማሰር፣ የሙስሊሞችን ንብረት ማውደም እና ማስለቀስ፣ የሙስሊሙን ቅርስ ማውድውም፣ ወዘተ ...!!

አይከብድምን??? ኡለማን በበቱ ከነልጆቹና ሚስቱ መግደል አያስጠላም??? ለፖሎቲካ ፍጆታ ሙስሊሞችን መጠቀም አያስጠላምን??? ሃይማኖት ካልተከበረልን፣ የዲን መሪየ ካልተከበረልኝ፤ አንድም የመንግስት አካል ሳይደርስለት ዝም ሲባል አያሳፍርምን??? አንድም የመንግስት አካል ሳይተነፍስ ከ 35 በላይ መስጂዶች ተቃጥሎ ዝም ሲባል፤ የሙስሊሙ አለም ቅርስ የሆነው የነጃሺ መስጂድ ሲፈርስ፣ ታድያ ብልፅግና ምናምን ምን ያረግልኛል??? የሙስሊም ወንድም/እህቶቼ መብት ካልተከበረ! መስጂድ ሲቃጠል ዝም ካለ፤ መንድነው ሃገር? ምንድነው መንግስት? ምንድነው ኢትዮጵያዊነት የሚባለው??? ሙስሊሙ ማህበረሰብ፣ ኡስታዞቹ እና የሙስሊሙ ህብረተሰብ ስለ ደረሰው በደል ደጋግመው ድምፃቸውን ቢያሰሙም የፌደራል መንግስቱም መንግስት በሚያሳፍር መልኩ ዝምታን መርጧል፤ ብልፅግና መጅሊስም ፀጥ ረጭ ብሏል።

በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል በሞጣ፣ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በባሌ ወዘተ፣ ከ 35 በላይ መጂዶች ሲቃጠሉ ዝምታን የመረጡ የመንግስት አካላት እና የመንግስት ሚዲያዎች፤ ነገር ግን አቢያተክርስትያናት ሳይቃጠሉም ተቃጠሉ ብለው ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች፣ ሚዲያዎች እና ማህበራት በተቃራኒው መልኩ ይዘግቡታል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ደግሞ በሰላማዊ እና አስተማሪ መንገድ ድምፅ ማሰማት ላይ ጎበዝ ነው። ይህ ድምፁ ደግሞ ዲንጋይ እና ጠመንጃ ካልሆነ ለማይቆረቁረው ለኢትዮ መንግስታዊ ቢሮክራሲ አሁንም ከቁብ አልተቆጠረም። እየቦታው ሙስሊሞችን በፖሎቲካ ስም ማሰር እና መግደል፣ እንዲሁም የሙስሊም ወጣቶችን እንቅስቃሰ ማቸናገፍ ሆኖዋል።

ከድምፁ በፊት መቅደም የነበረበትም የህዝበ ሙስሊሙ መሪዎች፣ ለጥቃቅን እና አነስተኛ አጀንዳዎች ሳይቀር በራቸው ክፍት የሆነውን የአሀገሪቷን ከፍተኛ መንግስታት በአስቸኳይ እንዲያናግሯቸው በመጠየቅ አፋጣኝ ውይይት በማድረግ መፍትሄ ላይ መድረስን መመካከር ነበር። እንደከዚህ በፊቱ መንግስታት፤ ሁሌም አደባባይ ወጥቶ በተመሳሳይ መልኩ በድምጽ መመለስ አግባብ አይመስለኝም፤ ምክኛቱም ያሁኑ መንግስት ፈጽሞ ከየተኛዉም በላይ ገዳይ እና የሰውን መብት ረጋች ከመሆኑ የተነሳ ከሱ ሊገኝ የሚችለው የበለጠ ግድያ እና እስር ብቻ ስለሆነ።

ከሰሞኑ ክስተትቶች እንደሰማነው ጉዳዩ ተራ ክስተት ሳይሆን የተቀናጀ የጅምላ እና የዘር ፍጅት (ሙስሊሙን በፖሎቲካ ስም እና ከሃገሪቱ በተለይም ከኦሮሚያ ክልል የማሳደድ እና የማደህየት) ሽብራዊ ተግባር መሆኑን አስረግጠን መናገር እንችላለን። የሃገሪቱ ሙስሊሞች ዘለቄታዊ ደህንነት አደጋ ውስጥ መግባቱ አሌ የማንለው አደጋ መሆኑን ሁሉም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መገንዘብ አለበት።

ኡለሞች በእስልምና፤ ይህ የማይባል ደረጃ ያላቸው፤ የህብረተሰቡ ቀንድ ሲሆኑ፤ አሁን ባለው መንግስት ግን፤ ተራ ሰው ሆኖ፤ በተራ ወታደር፤ በሚኖሩበት ዉስጥ ከነሙሉ በተሰባቸው እየተገደሉ ነው። የተገደሉትም ቢቻ ሳይሆኑ፤ አሁን በህወት ያሉትም፤ ምንም አይነት መንግስታዊ ዋስትና ሰለለላቸው ነገሩ እጅጉኑ አሳሳቢ ሆኖዋል። በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው፤ ግፍ፤ 99.8% በላይ የሙስሊሙን ህዝብ የጨፈጨፈ ነው። ይህ ማለት ደግሞ፤ በፖሎቲካ ስም፤ ሙስሊሞችን ማጥፋት ታቅደዋል ማለት ነው። በቅርብ ስለፈረሱት 35 መስጂዶች ብቻ ሳይሆን ባለፈው አስርና ሃያ አመታት ስለተደረገው ግፍና ጥቃት የጠለቀ መረጃ ለኡማው ማድረስ እና ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከዱሮም ባለፈ እርስበርስ በመደማመጥ ይኸን በኛ ላይ የተንጣለለውን ግፍ መዝለፍ አለበት። ጉዳዩ የክልልነት ስም ወይም የፖሎቲካ ክፍፍል ሳይሆን፤ በመላ አለም አለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች፤ መድረኮችን በመፍጠር፣ በመመካከር፤ እናም በተለይ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአረቡ አለም፣ አሜሪካን በጋራ በሚገኙበት መድረክ ጉዳዩን መዘርዘር እና መንግስት ከሃይማኖት እንዲወጣ ማድረግ መቻል አለበት።

.... ... ...

እናስ ለይቶ መገደል ካልቀረ፤ ብልጽና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ምኑ ነው???

የሚከተለው ታርት “የኢትዮጵያ የሲቪል ህጎች እና የሰባዓዊ መብት ጥሰቶች” 2017 ዕትም ከሚል የተወሰደ ነው::

አምባገነናዊ ፣ አሰልቺ ተቆጣጣሪው ፣ ጉልበተኛው ፣ ወይም ጨካኝ ሰው፣ ሁሉም ችግራቸው አንድ ነው። ሁል ጊዜም ግቦቻቸው ከህዝባቸው ህይወት እና ግብ ይልቅ አስፈላጊ ሆኖ ይታያቸዋል። አስቸጋሪ ፣ ግልፍተኛ ሰዎች፤ በዙሪያዎ እየመሩ ፣ ራስ ወዳድነትን ያሳድራሉ ፣ ያስፈራሩዎታል ፣ ፍላጎቶችን ያሳያሉ ፣ትዕዛዞችን ያባብሳሉ እና ስልጣናቸውን ያንሰራፋሉ። ጭቆናዎችን በማስፋፋት፣ የግዴታ ሃሳባቸውን ላማስፈን፤ ሰዎችን በኃይል ፣ በጭካኔ ወይም አጥፊ በሆነ መንገድ ይጠቀማሉ ፡፡ እነሱ ጨካኝ ፣ የዘፈቀደ ሃይል በሰዎች ላይ በመጠቀም፤ የብዙዎቻችን ሕይወት መንገድ አስቸጋሪ የሚያደርጉ ናቸው ፡፡ በአብዛኛው፤ እነሱ የሚረብሹ ፣ ግድየለሾች እና ሰብዓዊ ክብርን ዝቅ የሚያደርግ ናቸው። አምባገነናዊ መንግስታት፤ በጎራ በተከፋፈሉ ሰዎች ላይ፤ የጭቆናን ቀንበር እና ማንነትን የሚያዋርድ ዲርጊቶችን ያስከትሉባቸዋል። የተጨቆኑ ሰዎችን በኃይል ወይም ስልጣን በመጠቀም ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ ያጨናግፋሉ ፣ ወይም ቁጥጥር ይደረግባቸዋል።

2 views0 comments

Recent Posts

See All

Comments


Post: Blog2_Post
bottom of page