ያሳዝናል ያስለቅሳል!! ሙስሊም በበዛባት ሀገር ዲሞክራሲ አለ ተብሎ በሚወራባት ሀገር መስጂድ ማቃጠል፣ ኡለሞችን መግደል፣ ወጣቶችን መግደል እና ማሰር፣ የሙስሊሞችን ንብረት ማውደም እና ማስለቀስ፣ ወዘተ ...!!
አይከብድምን??? ኡለማን በበቱ ከነልጆቺና ሚስቱ መግደል አያስጠላም??? ለፖሎቲካ ፍጆታ ሙስሊሞችን መጠቀም አያስጠላምን??? ሃይማኖተ ካልተከበረልን፣ የዲን መሪየ ካልተከበረልኝ፤ አንድም የመንግስት አካል ሳይደርስለት ዝም ሲባል አያሳፍርምን??? አንድም የመንግስት አካል ሳይተነፍስ ከ 31 በላይ መስጂዶች ተቃጥሎ ዝም ሲባል፤ ታድያ ብልፅግና ምናምን ምን ያረግልኛል??? የሙስሊም ወንድም/እህቶቼ መብት ካልተከበረ! መስጂድ ሲቃጠል ዝም ካለ፤ መንድነው ሃገር? ምንድነው መንግስት? ምንድነው ኢትዮጵያዊነት የሚባለው??? ሙስሊሙ ማህበረሰብ፣ ኡስታዞቹ እና የሙስሊሙ ህብረተሰብ ስለ ደረሰው በደል ደጋግመው ድምፃቸውን ቢያሰሙም የፌደራል መንግስቱም መንግስት በሚያሳፍር መልኩ ዝምታን መርጧል፤ ብልፅግና መጅሊስም ፀጥ ረጭ ብሏል።
በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል በሞጣ፣ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ፣ በባሌ ወዘተ፣ ከ 31 በላይ መጂዶች ሲቃጠሉ ዝምታን የመረጡ የመንግስት አካላት እና የመንግስት ሚዲያዎች፤ ነገር ግን አቢያተክርስትያናት ሳይቃጠሉም ተቃጠሉ ብለው ሲዘግቡ የነበሩ ጋዜጠኞች፣ ሚዲያዎች እና ማህበራት በተቃራኒው መልኩ ይዘግቡታል።
ሙስሊሙ ማህበረሰብ ደግሞ በሰላማዊ እና አስተማሪ መንገድ ድምፅ ማሰማት ላይ ጎበዝ ነው። ይህ ድምፁ ደግሞ ዲንጋይ እና ጠመንጃ ካልሆነ ለማይቆረቁረው ለኢትዮ መንግስታዊ ቢሮክራሲ አሁንም ከቁብ አልተቆጠረም። እየቦታው ሙስሊሞችን በፖሎቲካ ስም ማሰር እና መግደል፣ እንዲሁም የሙስሊም ወጣቶችን እንቅስቃሰ ማቸናገፍ ሆኖዋል።
ከድምፁ በፊት መቅደም የነበረበትም የህዝበ ሙስሊሙ መሪዎች፣ ለጥቃቅን እና አነስተኛ አጀንዳዎች ሳይቀር በራቸው ክፍት የሆነውን የአሀገሪቷን ከፍተኛ መንግስታት በአስቸኳይ እንዲያናግሯቸው በመጠየቅ አፋጣኝ ውይይት በማድረግ መፍትሄ ላይ መድረስን መመካከር ነበር። እንደከዚህ በፊቱ መንግስታት፤ ሁሌም አደባባይ ወጥቶ በተመሳሳይ መልኩ በድምጽ መመለስ አግባብ አይመስለኝም፤ ምክኛቱም ያሁኑ መንግስት ፈጽሞ ከየተኛዉም በላይ ገዳይ እና የሰውን መብት ረጋች ከመሆኑ የተነሳ ከሱ ሊገኝ የሚችለው የበለጠ ግድያ እና እስር ብቻ ስለሆነ።
ከሰሞኑ ክስተትቶች እንደሰማነው ጉዳዩ ተራ ክስተት ሳይሆን የተቀናጀ የጅምላ እና የዘር ፍጅት (ሙስሊሙን በፖሎቲካ ስም እና ከሃገሪቱ በተለይም ከኦሮሚያ ክልል የማሳደድ እና የማደህየት) ሽብራዊ ተግባር መሆኑን አስረግጠን መናገር እንችላለን። የሃገሪቱ ሙስሊሞች ዘለቄታዊ ደህንነት አደጋ ውስጥ መግባቱ አሌ የማንለው አደጋ መሆኑን ሁሉም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መገንዘብ አለበ።
ኡለሞች በእስልምና፤ ይህ የማይባል ደረጃ ያላቸው፤ የህብረተሰቡ ቀንድ ሲሆኑ፤ አሁን ባለው መንግስት ግን፤ ተራ ሰው ሆኖ፤ በተራ ወታደር፤ በሚኖሩበት ዉስጥ ከነሙሉ በተሰባቸው እየተገደሉ ነው። የተገደሉትም ቢቻ ሳይሆኑ፤ አሁን በህወት ያሉትም፤ ምንም አይነት መንግስታዊ ዋስትና ሰለለላቸው ነገሩ እጅጉኑ አሳሳቢ ሆኖዋል። በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው፤ ግፍ፤ 99.8% በላይ የሙስሊሙን ህዝብ የጨፈጨፈ ነው። ይህ ማለት ደግሞ፤ በፖሎቲካ ስም፤ ሙስሊሞችን ማጥፋት ታቅደዋል ማለት ነው። በቅርብ ስለፈረሱት 35 መስጂዶች ብቻ ሳይሆን ባለፈው አስርና ሃያ አመታት ስለተደረገው ግፍና ጥቃት የጠለቀ መረጃ ለኡማው ማድረስ እና ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከዱሮም ባለፈ እርስበርስ በመደማመጥ ይኸን በኛ ላይ የተንጣለለውን ግፍ መዝለፍ አለበት። ጉዳዩ የክልልነት ስም ወይም የፖሎቲካ ክፍፍል ሳይሆን፤ በመላ አለም አለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች፤ መድረኮችን በመፍጠር፣ በመመካከር፤ እናም በተለይ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአረቡ አለም፣ አሜሪካን በጋራ በሚገኙበት መድረክ ጉዳዩን መዘርዘር እና መንግስት ከሃይማኖት እንዲወጣ ማድረግ መቻል አለበት።
.... ... ...
እናስ ለይቶ መገደል ካልቀረ፤ ብልጽና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ምኑ ነው???
2 የፌደራል መንግሰት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ምላሽ እንዲሰጥ ማድረግ። አጀንዳውን እንዳይስትም ሆነ በፖፀቲካዊ ጣልቃ ገብነት እንዳይከስም ቀነ ቀጠሮ ማስቀመጥ።በተለይ በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ ከቤተ መንግስት ደውሎ «ኡስታዝ እከሌ እንደዚህ አድርጉ.. » እያሉ የእጅ አዙር ጣልቃ መግባትን አለመቀበል።
3 የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን ሰብስቦ ስለ ጉዳዩ የተደረሰበትን መረጃ ማጋለጥ። ለዘመናት ይህ ማህበረሰብ ሲደርሰው የነበረው መረጃ የኢትዮ ሙስሊም ጠብ–አጫሪ እንደሆነ ተደርጎ ነው። ስለዚህ
4 ለሁሉም በአገራችን ለሚገኙ ኢንባሲዎች በየአለማቀፉ ቋንቋ የተጋረጠውን አደጋ በዝርዝር የሚገልፅ ደብዳቤ ፅፎ በየአድራሻቸው ማድረስ።
5 ለሁሉም በአገራችን ለሚገኙም ሆነ አለማቀፋዊ ለሆነ የሰብአዊ መብትሸ ተቋማት የተጋረጠውን አደጋ በዝርዝር ማስረዳት።
6 የውጭ ሚዲያዎችን እና የዜና ዐውታሮችን ጠርቶ ጉዳዩን በዝርዝር ማስረዳት እና ቦታው ድረስ ሄደው የደረሰውን እንዲዘግቡ ማድረግ።
አልጄዚራ፣ ቢቢሲ(የአማረኛው ሳይሆን እንግሊዘኛው)፣. ቲአርቲ፣ ወዘተ
Comments