ዛፉም እንዳይቆረጥ፣ ቅጠሉም እንዳይ ረግፍ፣ አንበሳዉም ይኑርበት!
አምባገነናዊ ፣ አሰልቺ ተቆጣጣሪው ፣ ጉልበተኛው ፣ ወይም ጨካኝ ሰው፣ ሁሉም ችግራቸው አንድ ነው። ሁል ጊዜም ግቦቻቸው ከህዝባቸው ህይወት እና ግብ ይልቅ አስፈላጊ ሆኖ ይታያቸዋል። አስቸጋሪ ፣ ግልፍተኛ ሰዎች፤ በዙሪያዎ እየመሩ ፣ ራስ ወዳድነትን ያሳድራሉ ፣ ያስፈራሩዎታል ፣ ፍላጎቶችን ያሳያሉ ፣ትዕዛዞችን ያባብሳሉ እና ስልጣናቸውን ያንሰራፋሉ። ጭቆናዎችን በማስፋፋት፣ የግዴታ ሃሳባቸውን ላማስፈን፤ ሰዎችን በኃይል ፣ በጭካኔ ወይም አጥፊ በሆነ መንገድ ይጠቀማሉ ፡፡ እነሱ ጨካኝ ፣ የዘፈቀደ ሃይል በሰዎች ላይ በመጠቀም፤ የብዙዎቻችን ሕይወት መንገድ አስቸጋሪ የሚያደርጉ ናቸው ፡፡ በአብዛኛው፤ እነሱ የሚረብሹ ፣ ግድየለሾች እና ሰብዓዊ ክብርን ዝቅ የሚያደርግ ናቸው። አምባገነናዊ መንግስታት፤ በጎራ በተከፋፈሉ ሰዎች ላይ፤ የጭቆናን ቀንበር እና ማንነትን የሚያዋርድ ዲርጊቶችን ያስከትሉባቸዋል። የተጨቆኑ ሰዎችን በኃይል ወይም ስልጣን በመጠቀም ፍትሀዊ ባልሆነ መንገድ ያጨናግፋሉ ፣ ወይም ቁጥጥር ይደረግባቸዋል።
ከቅርብ ጊዘ ክስተትቶች እንደሰማነው ጉዳዩ ተራ ክስተት ሳይሆን የተቀናጀ የጅምላ እና የዘር ፍጅት (ሙስሊሙን በፖሎቲካ ስም እና ከሃገሪቱ በተለይም ከከተሞች የማሳደድ እና የማደህየት) ሽብራዊ ተግባር መሆኑን አስረግጠን መናገር እንችላለን። የሃገሪቱ ሙስሊሞች ዘለቄታዊ ደህንነት አደጋ ውስጥ መግባቱ አሌ የማንለው አደጋ መሆኑን ሁሉም የሙስሊሙ ህብረተሰብ መገንዘብ አለበ።
ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ቦሃላ፤ አሃዳውያን፣ ፕሮ አብሲኒያዎቹ፤ የያኔው ወጣቶች እንኳን ሳይቀሩ ከሀምሳ አመት በኋላ አንገታቸውን ቀና ያደረገ እድል ያገኙ ይመስላሉ። የትናንት ልዮነቶቻቸውን፣ የማይታረቁ ስንጥቆቻቸውን፣ ይጠጌ አይነኬ አንድነታቸውን፣ ዘላቂያዊ ፕሮጀክት አድራጊ መሻቶቻቸውን ወዲያ ብለው ከግዳዩ የፖለቲካ ትርፍ ያገኙ ዘንድ የጥንብ አንሳ ህብረት ፈጥረው ሃጫሉ ግድያ ቦሃላ፤ ገዳዩን ከበው፣ ጉልበትም ብልሃትም አዋጥተው ጊዜያዊ ድል ላይ ናቸው። የሀጫሉን መገደልን ተከትሎ የተገኘው መና ሲና በረሃ ላይ እንደፈለቀ ውሃና እንደ ወረደ መና የሃምሳ አመት ርሀብን የከላ የድህረ የካቲት1966ን ጥም የቆረጠ ይሆን ዘንድ ርብርቡ ጡዞ ይነበባል።
ከሀጫሉ ግድያ ቦሃላ፤ በኦሮሚያ በሁሉም ቦታዎች የተከሰተው ታሪካዊና ቀውስ፤ ለነዚህ ኃይሎች እጅግም ድንቅ፣ ያልታሰበ ሰናይ እድልንና መሰባሰብን ፈጥሯል። የዚህ ስብስብ መጣበቂያ ሙጫው ደግሞ ማህበረ ቅዱሳንና የአማራ ብሄርተኝነት ነው።
የነዚህ ኃይሎች የጋራ ጠላታቸው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ነው። በእስልምና ላይ ልዩነታቸው ባላቸው የጥላቻ ድግሪ ደረጃና የባላንጣ መዘርዝር አለፍተ ቀደም ላይ ብቻ ነው። ይህም በመሆኑም የኢትዮጵያ ትርምስ፣ ቀውስ ሁሉ ተጠያቂው ይሄው የሙስሊሞች ኃይል ይሆን ዘንድ የጋራ ዘመቻ በማድረግ ላይ ናቸው ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እስከ ማዕዜኑ ይናገሩበት አፍ፣ ይጽፉበት ብዕር፣ ይታገሉበት ሞራል ይጡ ዘንድ እጅግ የተቀነባበረና የተባበረ የፕሮፓጋንዳ ሰለባና ማረገፊያ ተደርገው ለዘመናት ከርመዋል፡፡ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እጣ ፋንታ፤ በሰሞኑ የተደራጀና እጅግ ውስብስብ፤ በሆነው ፖሎቲካ መሰል ፕሮፓጋንዳ፤ ውጤት ላይ መቋጠሩ የማያጠያይቅበት ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስለኛል። እነዚህ ኃይሎች ይህን እድል አሟጦ አለመጠቀም ታርካዊ ስህተት መሆኑን ስለተረዱት፤ የተገኘውን እድል የሚያሰፉ ተጨማሪ ንትርክ መስማታችን አልቀረም። ይህ ጀብድ ደግሞ፤ በማህበረ ቅዱሳን አባላት በኩል የተሰራ መሆኑን ከተለያዩ ምንጮች ደርሰንበታል።
አንደኛ በኢትዮጵያውያን ሁሉ እስላም ክርስቲያን ሳይል መውደድን የተቸራቸው ተቀዳሚ ሙፍቴ ሸክ ኡመር ኢድሪስ ለውጡን ተከትሎ
ስብእናቸው እንዲጎላ እድሉን በማግኘታቸውና ‹ሰውነት ይቀድማል! ሰው ሁኑ!› በሚለው መርሃቸው በአገራችን ታሪካዊ ንጥር ሰብ ሆነዋል። እኒህ አባት የክብር ዶክትሬት ከማግኘትም አልፈው የእስልምና መጅሊስ ዋና ሃላፊ ናቸው። ዛረ ግን፤ የሙስሊሞቺ ዕልቂት አልገባቸው ብሎ እንደሆን አልገባኝም፤ ዝምታቸውን ከመቀጠል ይልቅ፤ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ባይ ሆኖዋል። እሳቸውን የሚወዳቸው ድፍን ኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆንም በተለየ መልኩ አሃዳውያን፣ ዲ/ን ዳኒኤል ክብረትን ይዞ በተዋረድ መምህር ትርምስን ከመፍጠር አላዳናቸውም።
የአብይ አህመድ አስተዳደርም ለሙፍቲው የፈጠረው ቀረቤታ መልካም ገጽታ ግንባታ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ምንም እንኳን ተቀዳሚ ሙፍቲው የሁላችንንም ቀልብ ማሸነፍ የሚችሉ አባት ቢሆኑም ይህ ግለሰባዊ ስብዕና ግንባታ በመንግሥት፣ በአሃዳውያን፣ በማህበረቅዱሳን፤ እና በሰፊው የሙስሊሙ ህብረተሰብ በኩል፤ አጥጋቢ አልነበረም።
አቅጣጫው አንድም ተቀዳሚ ሙፍቲውንና ሱፊያውን በመያዝ በውሀቢያነት ስም ጽንፈኛነት ተሰጥቶት ሊወገድ የሚገባውን የሙስሊም ኃይል መፈረካከስ፣ መበተንና ማጥቃት አልፎም ማጥፋት የሚቻልበት ሁነኛ ዘዴ ሲሆን፣ ለላኛውና አደገኛው ፕላናቸው፤ የሰሞኑ ሽፍጥ ግን ኢማሞችን በመግደል ነቅቻለሁ ያለውን የሙስሊሙን ኃይል ለአንደና ለመጨረሻ ጊዜ መቅበር ነው፡፡ ሀጫሉ በተገደለ እለት ቄሮ ነፍጠኛ ገደለብኝ ብሎ እንደወጣው ሁሉ፤ አሁን ደግሞ፤ የሙስሊሞቹን ዋና አገልጋይን፤ በመግደል ውሐብያው ውይም ሱፊያው ገደላቸው ብሎ ከሃይማኖታዊው ኃይል እስከ አምሃራውና አሃዳዊው አልፎም ተራው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በነቂስ እሪ ብሎ ሲወጣ ለማጫረስ ነው። ያኔ የሙስሊሙ ማህበረሰብ፣ ነቃሁ ያለ ሙስሊም ሁሉ በአሸባሪነት ስም ከጀዋር ሙሃመድ ጋር ቃሊቲ እንዲገናኙ በማድረግ በድህረ 2004 በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ሁለንተናዊ ውድመት እንዲቀጥል ይደረጋል።
በእስልምና ላይ ለማድረስ ከተሳሉት ጥቃቶች ለላኛው፤ የሃይማኖት ስብዕናቸው የጎላ ግን በብሄር ደረጃ ወደ አንድ የብሄር ቋት ያዘነበሉ ወይም በዚያ ብሄር ቁመና ልክ እንዲሳሉ ትግል የተደረገባቸው ወይም ለአንድ ብሄር ወይም የፖለቲካ አሰላለፍ ግልጽ ወገንተኝነት አላቸው ተብለው የተገመቱ የእስልምና እውቅ ሰዎች ሌላኛዎቹ ዒላማዎች መሆናቸውን ሰምተናል። ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ እስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎችን ለማስገደል ጉምጉምታ መኖሩ እየተሰማ ነው። የሰሞኑ የማኅበራዊ ሚዲያ፤ እነ ሔኖክ የሺጥላ “አህመዲን ይገደላል!”የሚሉት፤ ፍንጭም ሆነ የኢትዮ 360 ጠበቅ ያለ ፕሮፓጋንዳ የዚህ ሴራ ጭስ መሆኑን ስንቶቻችሁ ተረድታችሁት ይሆን?
እነዚህን ሰዎች በቀጥታ መግደል በሃጫሉ ግድያ ላልተማረው የኦሮሞ ሙስሊም ወጣትና የሃይማኖቱ ጎራዎች፤ ሆነ በፖለቲካ ሴራ እጅጉን ኋላ ለቀረው ለጠቅላላው የሙስሊሙ ህዝብ፤ እጅጉን ቀይ መስመር በመሆኑ የሃጫሉን ግድያ መሳይ ከጫፍ እስከ ጫፍ የሚታፈስ መሆኑን ለመተንበይ አያዳግትም። አህመዲንን፣ ያሲንና አቡበከርን አይደለም፤ መለስተኛ እውቅና ያላቸውን የሙስሊም ምሁራንን ለመግደል ወደ ኋላ እንደማይሉ ባውቃቸውም በዚህኛው ዙር ግን የመጀመሪያ ሰለባ፤ ማን ይሆን አልገባኝም።
ከአመታት በፊት ደሴ ላይ የወያነ መንግሥት፤ በመንግሥት ውሥጥ በተሰገሰገው ኃይል ሸክ ኑሩ የተባሉትን ኢማም በመግደል የሰሩበትን ጫወታ የረሳው ይመስላል። ለዚህም ነው አሁንም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ሚወተወቱት።
ከሁሉም በላይ ደግሞ፤ የኡስታዝ ራያ አባመጫ ልያሳስበን ይገባል። ኡስታዝ ራያ፤ በኦሮሞ ህብረተሰብ ዉስጥ፤ እጅጉኑ ተወዳጅና የተከበረ ሰው ከመሆኑ የተነሳ፤ ባሁኑ ሰዓት ያለውን ለጀዋር ሙሃመድ፤ የፖሎቲካ ውዝግብ አቅጣጫውን ለማሳት ሲሉ፤ ሊያስገድሉት ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ። አሁን ያለው መንግስት፤ የኦሮሞ ህዝብ ሰላሙን አግኝቶ እንዲኖር ስለማይፈልግ፤ በህብረተሰቡ ዉስጥ ታወዳጁን ሰው ግድሎ፤ አሁንም ህዝቡን ለእልቂት ማድረግ ይፈልጋሉ። በተጨማሪም፤ ከሃጫሉ በፊት፤ አብይ አህመድ፤ ኡስታዝ ራያን በቢሮው ጠርቶት እንዳስፈራራ ሰምተን ነበር ስለሆነ።
ከሁሉም በላይ እነን የሚያሳስበኝ፤ የሙስሊሙ ህብረተሰብ እስከሁን ድረስ ከፖሎትካ መጠቀሚያነት በጻ መሆን አለመቻሉ ነው። በየዘመናቱ መቶ ሚያልፉ መንግስታት ሁሉ፤ ሙስሊሙን ህብረተሰብ እንደ መጠቀሚያ አድርጎ፤ እርስ በርሳቸው፤ አባልቶ፤ ለራሳቸው ስልጣን ይይዛሉ።
ስለዚህም፤ የሙስሊሙ ህብረተሰብ፤ ከሚንጊዘውም በላይ፤ ልዩነቱን አጥቦ፤ አንድነቱን አጠናክሮ፤ አንዳችም ለጠላቱ መንገድ ሳይከፍት፤ ሊደርስ የሚችለውን አደጋን መከላከል አለበት።
Comments